እናት መረጃ - Enat Mereja
ကျန်းမာရေး နှင့် ကြံ့ခိုင်ရေး | 6.0MB
ይህ የሞባይል መገልገያ ነብሰጡሮችና እናቶችን ስለቅድመ ወሊድ ፣ ድህረ ወሊድና ወሊድ የጤና ክትትሎች ለማስተማር የተዘጋጀ ነው። ለሞት የሚያበቁ አደገኛ ምልክቶችን አውቀው በግዜ የጤና አገልግሎት እንዲሹም ያቀደ ነው። ይህ መገልገያ በውስጡ የያዘው መረጃ
1. ስለእርግዝና: ምልክት፣ ስሜቶችና ማቅለያ መንገዶች፤ አመጋገብ፤ አደገኛ ምልክቶችና ውስብስብ ችግሮች
2. ቅድመወሊድ: ስለቀጠሮዎች ጊዜና በየቀጠሮው ስለሚኖር ምርመራ፤ አስፈላጊነቱና ጥቅሙ
3. የፅንስ እድገት: በየወሩ ፅንሱ እንዴት እንደሚያድግ፤ በእናትየውና በፅንሱ ላይ ስለሚታዩ ለውጦች፤ የፅንስ እድገት ምስል
4. ወሊድ: ስለምጥና በወሊድ ሰአት ሊከሰቱ ስለሚችሉ ያልታሰቡ ችግሮች
5. የአራስ ልጅ እንክብካቤ: አደገኛ ምልክቶች፤ ጡት ማጥባትና ማለብ፤ለቅሶን መረዳት
6. ድህረ ወሊድ: ቀጠሮዎች፣ እርግዝናን መከላከልና እራስን መንከባከብ
7. ከ 5 አመት በታች: አስፈላጊ እንክብካቤዎች፤ የእድገት ክትትል፤ተጨማሪ ምግብ፤ ቁልፍ መልእክቶች
8. ክትባት: ቀጠሮዎች፤ የክትባት አይነትና ጥቅም
በሌላ በኩል ሞባይል መገልገያው
1. የወሊድ ቀንን ያሰላል
2. ለመጨረሻ ግዜ የወር አበባ የታየበትን ቀን መሰረት አድርጎ በየወሩ የፅንስ ክትትልና የቅድመወሊድ ቀጠሮ ቀን ማስታወሻ ይልካል
3. የልጅ እድሜን ያሰላል
4. ልጅ የተወለደበትን ቀን መሰረት አድርጎ የክትባትና የድህረ ወሊድ ቀጠሮ ቀን ማስታወሻ ይልካል
updated UI
အပ်ဒိတ်လုပ်ပြီး: 2019-06-27
လက်ရှိဗားရှင်း: 1.1
Android လိုအပ်သည်: Android 4.0 or later